የማንቺስተር ዩናይትዱ አዲስ አለቃ ኦማር በራዳ ማናቸው? ስራቸውስ ምን ይሆናል?
ማንቺስተር ዩናይትድ ከ2 ወራት ገደማ በፊት የሲቲ ፈት ቦል ግሩኘ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆነውን ኦማር በራዳን ሹመት ይፋ በማድረግ ደጋፊዎቻቸውን ' ሰርኘራይዝ' ማድረጋቸው አይዘነጋም።
ኦማር በራዳ ማነው?
ኦማር የማንቺስተር ዩናይትድ ዋና ስራ አስኪያጅ( cheif executive officer/ CEO) ሆኖ ከመቀጠሩ በፊት የሲቲ ፉት ቦል ግሩኘ CEO በመሆን እያገለገለ ይገኝ ነበር፤ ሲቲ ፉት ቦል ግሩኘ ማንቺስተር ሲቲን ጨምሮ ሌሎች 12 ክለቦች በስሩ የያዘ ተቋም ነው።
ኦማር ሲቲን በ2011 ሲቲን ሲቀላቀል የክለቡ አለምአቀፍ ቢዝነስ ልማት መሪ በመሆን ነበር። የሲቲ ግሩኘ CEO ከመሆኑ በፊት በማንቺስተር ሲቲ በዳይሬክተር ኦፍ ፓርትነር ሴልስ ፣ በክለቡ ምክትል ኘሬዝዳንት የንግድ ዳይሬክተር እንዲሁም የክለቡ ቺፍ ኦኘሬቲንግ ኦፊሰር በመሆን ሰርቷል።
በ2020ም የሲቲ ፉት ቦል ግሩኘ አመራር ሆኖ ተሾመ።
ልክ እንደ ሌሎቹ የማንቺስተር ሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ኦማር ባርሴሎና ስኬታማ በነበረባቸው አመታት በክለቡ መስራት ችሏል፤ ግለሰቡ ግን እንደሌሎቹ ካታላን አይደለም፤ የዘር ግንዱ ከሞሮኮ የሚመዘዝ ፈረንሳዊ ነው።
በክለብ ውስጥ ' CEO' ምን ያህል ወሳኝ ነው?
የእግር ኳስ ክለብን ቢዝነስ ለማስኬድ ሁለት ክፍሎች አሉ።
አንደኛው ስፖርታዊ ጎን ሲሆን ይህም ዝውውሮችን መከታተል፣ የኮንትራት ስምምነቶችን መፈፀምን ያጠቃልላል። ሌላኛው ጎን ደግሞ ቀሪ የክለቡን የስራ ሂደቶች የሚያካትት ነው። ለምሳሌ እንደ መሰረተ ልማት፣ ስፖንሰር ሺኘ እና ሌሎች ጉዳዮች በዚህ ስር ልናካታቸው እንችላለን፤ ከ1000 በላይ ሰዎችም በስራው ላይ ይሳተፋሉ።
ኤዱ ዱዋርድ(2012-2022) የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ በነበረበት ወቅት ይተች የነበረበው በስፖርቱ ምንም አይነት የጀርባ ታሪክ ሳይኖረው በርካታ ስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ ጠለቅ ያለ ተሳትፎ በማድረጉ እንደነበር ይታወሳል።
ሆኖም አሁን ላይ የዩናይትድ መዋቅር የሚታይ ለውጥ እያካሄደ ይገኛል።
የሰር ጂም ራትክሊፉ INEOS የክለቡን 25 መቶኛ ድርሻ ለመግዛት ከተስማማ በኋላ የሪቻርድ አርኖልድን ቦታ ለመተካት ተቋሙ ኦማርን ሲከታተለው ቆይቷል፤ ኦማር እንዲሾም ጥቆማ ያቀረቡት ደግሞ ግሌዘሮች ናቸው።
ኦማር የክለቡ የቢዝነስም ሆነ የስፖርቲንግ መስክ ዋና ስራ አስኪያጅ እንዲሆን ብሎም ተጠሪነቱ ለዩናይትድ ባለቤቶች ሆኖ በክለቡ ቦርድ ኦፍ ዳይሬክተርስ ቦታ እንዲኖረው ታቅዷል።
ይሄ ለማንቺስተር ዩናይትድ ምን ማለት ነው?
ይሄ ሹመት በክለቡ ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ነው።
ምንም እንኳን ግሌዘሮች አሁንም የክለቡን ከፍተኛውን ድርሻ ቢይዙም አቅም ያለው ዋና ስራ አስኪያጅ ከጎረቤታቸው ሲቲ መውሰዳቸው ነገሮች እየተለወጡ እንደሆነ ማሳያ ሊሆን ይችላል።
አሁን እንግዲህ ክለቡ ለውጥ እንዲያመጣ ልምድ ያለው አመራር ተሹሞለታል፤ ለውጥ ይመጣል ወይ የሚለውን በሂደት የምናየው ይሆናል።
ዘአትሌቲክ ኤክስክሉሲቭ
© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu