የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ከሚቀጥለው የውድድር ዘመን ጀምሮ በበፊቱ ፎርማት እንደማይቀጥል ይፋ ሆኗል፤ አዲሱ ፎርማትም እንደሚከተለው ነው።
በቅድሚያ 32 ክለቦችን የሚያሳትፈው ሻምፒዮንስ ሊግ አባላቱን ወደ 36 የሚያሳድግ ይሆናል፤ አዲሱ ፎርማት በምድብ ጨዋታዎች ፋንታ የሊግ ፎርማት የሚኖረው ይሆናል፤ አራት ቋት የሚኖር ሲሆን የቋቱ ምደባ የሚካሄደው በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር የክለቦች ደረጃ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ይሆናል፤ አንድ ቡድን ከአራቱ ቋት ከተወጣጡ ሁለት ሁለት ቡድኖች ጋር በአጠቃላይ ስምንት ጨዋታዎችን ግማሹን በሜዳው ግማሹን ከሜዳው ውጭ ያደርግና በስተመጨረሻም ልክ እንደ ሊግ ከ1-36 ደረጃ የሚሰራ ይሆናል።
በመቀጠል ከ1-8 የወጡት ቡድኖች በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፍ(16) ውስጥ የሚገቡ ሲሆን ከ9ኛ እስከ 16ኛ ያሉ ቡድኖች ከ17 እስከ 24ኛ ከሚገኙ ቡድኖች ጋር ኘሌይ ኦፍ በሜዳ እና ከሜዳ ውጭ እንዲጫወቱ ይደለደላሉ፤ በድምር ውጤት ያሸንፈቱም 8 ውስጥ ይገባሉ።
በአንፃሩ ከ25-36 ሚጨርሱት ቡድኖች ከውድድሩ በቀጥታ የሚሰናበቱ ሲሆን፤ ወደ ኢሮፓ ሊግ መውረድ ሚባል ነገር የለም፤ ከሁሉም የአውሮፓ ውድድሮች ነው የሚሰናበቱት።
ከ16ቱ በመቀጠል ሩብ ፍፃሜ ፣ ግማሽ ፍፃሜ እና ፍፃሜ እያለ በበፊቱ ፎርማት የሚቀጥል ይሆናል።
ይህ አዲስ ፎርማት በኢሮፓ ሊግም ሆነ በኮንፍረንስ ሊግ ተግባራዊ ይሆናል።
ምንጭ: የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ይፋዊ ገፅ
© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu