የሊጉ አክስዮን ማህበር በዶ/ር ጋሻው አማካኝነት ጥልቅ ጥናት አስጠንቷል የጥናቱ አጥኚ ዶ/ር ጋሻው በታውሰን ዩኒቨርስቲ በተባባሪ ኘሮፌሰርነት እንዲሁም በጀርመን ሙኒክ የቢዝነስ ስኩል የዶክቶራል ዲግሪ አማካሪ በመሆን እየሰሩ ይገኛሉ።
በጥናቱ መሰረትም የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ኘሪምየር ሊግ እግር ኳስ ተጫዋቾች አማካይ ወርሀዊ ደሞዝ 2667 ዶላር( 143,750 ብር አካባቢ) ሲሆን ይህም ሊጉን ለተጫዋቾች ከፍተኛ ደሞዝ የሚከፍል ሶስተኛው የአፍሪካ ሊግ አድርጎታል። ዝርዝሩንም ስንመለከት
1/ ደቡብ አፍሪካ- 7500 ዶላር( 404,250 ብር አካባቢ)
2/ ሞሮኮ- 7000 ዶላር( 375,595 ብር አካባቢ)
3/ ኢትዮጵያ- 2667 ዶላር( 143,750 ብር አካባቢ)
4/ ናይጄሪያ- 1,250 ዶላር( 67,375 ብር አካባቢ)
5/ጋና- 1000 ዶላር( 53,656 ብር አካባቢ)
6/ ኬንያ- 800 ዶላር( 42,925 ብር አካባቢ)
....እያለ ይቀጥላል። ( እዚህ ጋር የግብፅን ማወቅ ስላልተቻለ አልተካተተም)
ከዚህ በተጨማሪም ሁሉም የሊጉ ክለቦች በሚባል መልኩ ጤናማ የፋይናንስ አስተዳደር እንደሌላቸው የሚያሳይ ማስረጃም ወጥቷል። ይህም ክለቦች ከ70-80 መቶኛ የሚሆነውን በጀታቸውን በሙሉ ለደሞዝ ማዋላቸው ነው። ጤናማ የፋይናንስ አስተዳደር ያለው ክለብ ግን ከበጀቱ ለደሞዝ ወጭ የሚያደርገው ከ60-70 ባለው ውስጥ መሆን ይኖርበታል።
ሌላው በጥናቱ የተረጋገጠው ነገር ደግም አንዳንድ የሊጉ ክለቦች በስማቸው የተመዘገበ የባንክ አካውንት እንደሌላቸው ነው።
ጥናቱ በሊጉ ያሉትን ችግሮች ብቻ ሳይሆን ምክረሀሳቦችም ይዟል ያሉት ዶ/ር ጋሻው ጥናቱን በአግባቡ መሬት ላይ ማውረድ ከተቻለ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ለውጥ አስተዋፅኦ ማበርከት የሚችል ነው ብለዋል።
ጥናቱ ሌሎች ሰፊ አንኳር ነጥቦች የያዘ በመሆኑ በሌሎች ዘገባዎችም እንመለሰብታለን።
© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu