Nav And Top Bar

አሌሀንድሮ ጋርናቾ: የማንቺስተር ዩናይትዱ" Electric Entertainer"  ከየት ወዴት ( ቅምሻ)

አሌሀንድሮ ጋርናቾ: የማንቺስተር ዩናይትዱ" Electric Entertainer"  ከየት ወዴት

አሌሀንድሮ ጋርናቾ ለወሩ ምርጥ ጎል ገና ከአሁኑ የታጨች ' bicycle kick' ማስቆጠሩ ይታወሳል፤ የጋርናቾ የቅርብ ተከታታዮች እንደዛች አይነት ልዩ የሆነች ጎል ሲያስቆጥር ሲያዩ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

ማንቺስተር ዩናይትድ የእያንዳንዱ ቡድናቸውን እንቅስቃሴ ሪከርድ አድርገው ያስቀምጣሉ፤ እናም ጋርናቾ ያቺን ውብ ጎል ካስቆጠረ በኋላ በማግስቱ " በዊጋን ያስቆጠራትን ጎል ደገመው" ሲሉ ነበር የተናገሩት፤ ይሄን ያሉትም ከ2 አመት በፊት እንደዛችው አይነት ልዩ ጎል በ17 አመት በታች ውድድር ላይ አስቆጥሮ ስለነበር ነው።

የዩናይትድ የአካዳሚው ዳይሬክተር የሆኑት ኒክ ኮክስ  "ሁሌ እንቅስቃሴዎቻችንን ሪከርድ እናደርጋለን፤  ነገር ግን በዊጋን የነበረው ዝናብ ከባድ ስለነበር ለተንታኞች መገልገያ የተዘጋጀው ካሜራ እየሰራ አልነበረም፤ ሁለት ጎል አስቆጥሮ፤ የመጀመሪያው ጎል እኮ ተቀርጿል፤ ሁለተኛዋ( ልዩዋ) ጎል ግን ልትቀረፅ አልቻለችም፤ ይሄንን ታምናላችሁ" ሲል በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ያስታውሳል።


ጋርናቾ በየሳምንቱ ጨዋታዎችን እየጀመረ በዩናይትድ ጥሩ የሚባል ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም በኤቨርተኑ ጨዋታ ላይ በአንድ ጨዋታ ሁለት የፍፁም ቅጣት ምቶችን ማስገኘት የቻለ የመጀመሪያው የዩናይትድ ተጫዋቾ መሆን ችሎ እንደነበር ይታወሳል።

ዩናይትድ ማድሪድ ስለተወለደው አርጀንቲናዊ የስካውቲንግ ሪፖርቶች ይደርሱት የነበረው ገና የ14 አመት ታዳጊ ሳለ ነበር፤ ዩናይትድ በ2016( እ.ኤ.አ) በአውሮፓ ሰፊ የምልመላ መዋቅር ዘርግቶ ተጫዋቾችን ሲከታተል አንደኛው የተመደበው መልማይም ሄራርዶ ጉዝማን ይሰኛል፤ ሄራርዶ የአትሌቲኮ የምልመላ ቡድን ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን ሰርቷል።

✨ይህ ግለሰብ ጋርናቾ 10 አመቱ ሳለ ጀምሮ ያውቀዋል፤ ያለውን በራስ መተማመንም የሚያደንቅለት ሲሆን ወዲያው ነው ለአትሌቲኮ ያስፈረመው። ጉዝማን ከነጋርናቾ ቤት በ500 ሜትር ርቀት ላይ ነበር የሚኖረው፤ ይህም በጥሩ ሁኔታ እንዲከታተለው አግዞታል። የጉዝማን ልጆች እና ጋርናቾ በአንድ የእግር ኳስ ማሰልጠኛ ነበር ይሰለጥኑ የነበሩት፤ በዚህም የተነሳ ያውቀዋል። በፍጥነት ተፅእኖ የመፍጠር አቅም ያለው ጋርናቾ በ2005 11 አመቱ ሳለ የአትሌቲኮ ወጥ ጎል አስቆጣሪ እና ወሳኝ ተጫዋች መሆን ቻለ።

✨" ሄራርዶ 'Mr Foot ball' ነው እና ሀሉም በስፔን ያለ ሰው ያውቀዋል" ይላል ኮክስ፤ ጥሩ የሆነ ግንኙነት የመመስረት ባህርይ ያለው ሲሆን ታዳጊ ተጫዋቾችን በያገባኛል ስሜት ትኩረት ሰጥቶ ይከታተላል" ሲልም አክሎ ይናገራል። ከዚህ በተጨማሪም ሄራርዶ የኛን የምልመላ ቡድን መቀላቀል እጅጉኑ ጠቅሞናል ሲል ያነሳል።

ጋርናቾን ወደ እንግሊዝ ለማምጣት ስለተጫዋቹ የሚያውቅ የውስጥ አዋቂ ግድ ይል ነበር፤ ጉዝማን ጋርናቾ በአትሌቲ ደስተኛ እንዳልነበር ያውቃል፤ ኮንትራቱም በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ተረድቷል። በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ሁሉም ቤቱ ሲቀመጥ ጋርናቾ እና ጉዝማን በተመሳሳይ ጂም ቤት ነበር የአካል ብቃት እንቅስቃሴያቸውን ይከውኑ የነበረው፤ ስለዚህ ጋርናቾ ምን ያህል ታትሮ እንደሚሰራ ለመመልከት እድሉን ማግኘት ችሏል። ሌሎች የስፔን ክለቦች ተጫዋቹን ፈልገውታል፤ ከእንግሊዝ ግን ከዩናይትድ ውጭ ማንም አልነበረም።

ጋርናቾ ለዩናይትድ ብቁ ነው ወይ የሚለውን ለማወቅ በሱ እድሜ ካሉ እና በሱ ቦታ ከሚጫወቱ ዩናይትድ እይታ ውስጥ ከሚገኙ ተጫዋቾች ጋር ማነፃፀሩ አስፈላጊ ነበር፤ ይሄንንም የአካዳሚው የምልመላ ቡድን የሆነው ዴቭ ሀሪሰን እና የቡድኑ ዳይሬክተር ኦፍ ስካውቲንግ የሆነው ስቲቭ ብራውን ሰርተውታል።

ዘ አትሌቲክ ኤክስክሉሲቭ

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu