Nav And Top Bar

የኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ ክለቦች የሶስት ፈረሶች እሽቅድምድም መስሏል!

ብርቱ ፉክክር እየታየበት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ ሶስት ክለቦች አንገት ለ አንገት ተናንቀው ይገኙበታል። ዛሬ መሪዎቹ መከላከያ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የተገናኙ ሲሆን ሁለቱም አንደኛ ላይ የመቀመጥ እድሉን ሳይጠቀሙበት አቻ ወጥተዋል፤ ንግድ ባንክ በአንፃሩ ተጠቃሚ ሆኗል።

ዘንድሮ ሊጉን ተቀላቅሎ ትልልቅ ተጫዋቾችን በማዘዋወር ብርቱ ተፎካካሪ ሆኖ የቀረበው ንግድ ባንክ ሊጉን በ40 ነጥብ እና በ37 የጎል ክፍያ እየመራ ሲገኝ መቻል በአንፃሩ በተመሳሳይ 40 ነጥብ እና በ26 የጎል ክፍያ ይከተላል።

የአምና ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመረዎቹ በሁለት ነጥብ ርቆ በ38 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የእነዚህ ሶስት ክለቦች ተቀራራቢ ነጥብ ላይ መገኘት ቀጣይ የሊጉን ጨዋታዎች ተጠበቂ እንደሚያደርጋቸው ይጠበቃል።

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu