Nav And Top Bar

የኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ምን ይመስል ነበር?

የሶስት ክለቦች የሻምፒዮናነት ብርቱ ፉክክር እየተደረገበት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትላንት ተጠናቀዋል።

በሳምንቱ ተጠባቂ የነበረው ጨዋታ መሪዎቹ ተርታ ሚገኙትን ቅዱስ ጊዮርጊስ እና መቻልን ያገናኘ ሲሆን ሁለቱም ላለመሸናነፍ በታክቲክ የታጠረ ጨዋታ አድርገው ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።

ከመሪዎቹ አንዱ የሆነው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ከዚ ውጤት ተጠቃሚ መሆን ችሏል። ከዚህ በተጨማሪም የራሱን የቤት ስራ ሀምበርቾን በሰፊ የጎል ልዩነት በማሸነፍ በሚገባ ሰርቷል።

ተመጣጣኝ ሚባል ፉክክር የታየበት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከነማ ያደረጉት ሲሆን በኢትዮጵያ ቡና የ3ለ 2 አሸናፊነት ተጠናቋል፤ነጥቡን 33 በማድረስም ከመሪዎቹ ብዙም ሳይርቅ መቀመጥ ችሏል።

በ20ኛው ሳምንት 19 ጎሎች የተቆጠሩ ሲሆን ይህም ማለት በአማካይ በየጨዋታው 2.3~2 ጎሎች ሲቆጠሩ እንደነበር ያሳያል።

ሊጉን ንግድ ባንክ በ40 ነጥብ ሲመራ መቻል በተመሳሳይ 40 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ( ንግድ ባንክ- 17, መቻል-8) ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሁለት ነጥብ ዝቅ ብሎ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ወልቂጤ ከነማ፣ ሻሸመኔ ከነማ እና ሀምበሪቾ ደግሞ ወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኙ ክለቦች ናቸው። ሀምበሪቾ 27 የጎል እዳ እና 7 ነጥብ ይዞ የሊጉ ደካማ ቡድን መሆኑን ለመመልከት ተችሏል።

የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ደረጃ የሀዋሳ ከነማው ኤርትራዊው አሊ ሱሌይማን በ11 ጎሎች ሲመራ የድሬደዋው ቻርልስ ሙሴጌ በ9 ጎሎች ይከተላል።

በ21ኛ ሳምንት ባህርዳር ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ አርብ ምሽት 1:00 ሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። እሁድ ምሽት 1:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከነማ ሚያደርጉት ጨዋታም ብርቱ ፉክክር ሊደረግበት እንደሚችል ይጠበቃል። ሀምበርቾ ከሳምንት ሳምንት እያሳየ ካለው ደካማ ብቃት አንፃር ፋሲል ከነማ ከ ሀምበርቾ ሚያደርጉት ጨዋታ በፋሲል ሰፊ የጎል ልዩነት አሸናፊነት ሊጠናቀቅ እንደሚችል መገመት ይቻላል።

ዘገባውን ስናጠናቅር የኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ ይፋዊ ገፅን እንዲሁም ሶከር ኢትዮጵያን እንደምንጭነት ተጠቅመናል።

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu