የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ አርሰናል እና ባየርሙኒክን ያገናኛል፤ ሁለቱ ክለቦች ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው ጨዋታዎች ውጤት መለኪያ የባየር ሙኒክ የበላይነት ቢንፀባረቅም በወቅታዊ አቋም ግን ብዙዎች የአሸናፊነት ቅድመ-ግምቱን ለአርሰናል እየሰጡ ይገኛሉ።
የኦኘታ ሱፐር ኮምፒውተር ዛሬ የሚደረገውን ተጠባቂ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ የአሸናፊነት ቅድመ ግምት ለአርሰናል ሰጥቷል፤ እንደ ሱፐር ኮምፒውተሩ ከሆነ አርሰናል 51.5 መቶኛ ጨዋታውን የማሸነፍ ቅድመ-ግምት የተሰጠው ሲሆን ባየር ሙኒክ በአንፃሩ 24.1 መቶኛ የማሸነፍ ግምት ተሰቶታል።
በሻምፒዮንስ ሊጉ ከፍተኛ የሆነ የጎል አስተዋፅኦ ያለው ሳካ ነው፤ 3 ጎል እና 4 አሲስት አለው።
ሌላኛው አጥቂ ሀቨርትዝ 1 ጎል ብቻ ያለው ቢሆንም የአርሰናልን ኘሬስ በመምራት በኩል ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
በጨዋታው ላይ የማይገኘው ብቸኛው ተጫዋች ከጉዳት በማገገም ላይ ያለው ጁርያን ቲምበር ነው።
አርሰናል በቅርብ አመታት በአህጉር አቀፍ ደረጃ ጥሩ የሚባል ልምድ ባይኖራቸውም በቀውስ ላይ የሚገኘውን ባየርሙኒክ እንደሚያሸንፉ ቅድመ-ግምት ተሰቷቸዋል።
ባቫርያኑ በኢሜሬትስ ማስቆጠር የሚቀናውን ሀሪ ኬንን ይዘው ነው ወደ ለንደን ያቀኑት፤ ሀሪኬን በኢሜሪትስ 5 ጎሎች ያስቆጠረ ሲሆን ይህም ከጄሚ ቫርዲ እና ከዲያጎ ጆታ ጋር በመሆን ኤሚሬትስ ላይ ብዙ ጎል ያገባ የተቃራኒ ቡድን ተጫዋች ያደርገዋል።
ኑዌር፣ ኮማን፣ ሳኔ እና ማዙሪ የመሰለፋቸው ነገር አጠራጣሪ ነው። ራፍየል ጉሬሮ ከባት ጉዳት አገግሞ ለጨዋታው ብቁ መሆኑ ተረጋግጧል።
ባየርሙኒክ ባለፉት 6 ከእንግሊዝ ክለቦች ጋር በተደረጉ የሜዳ ውጭ ጨዋታዎች የተሸነፉት በአንዱ ብቻ ነው፤ ይሄንንም ማድረግ የቻለው ማንቺስተር ሲቲ (አምና) ነው።
አርሰናል በሁሉም ውድድሮች ባለፉት ተከታታይ 7 ጨዋታዎች አልተሸነፈም።
ባየርሙኒክ በአርሰናል ተሸንፎ ከውድድሩ ውጭ ሚሆን ከሆነ ለተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ ከሩብ ፍፃሜ የመሰናበት እጣ ይገጥመዋል።
ዛሬ ምን ይፈጠር ይሆን? አብረን የምናየው ይሆናል...
© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu