እጅግ አዝናኝ ከነበሩት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች በኋላ የተሰጡ አስተያየቶች:
አርሰናል ከ ባየርሙኒክ
ማይክል አርቴታ
"ጨዋታው የተለያዩ አጋጣሚዎች አሉት፤ ጥሩ አጀማመር ነበረን፤ ከጎሉ በኋላ ቤን ኋይት ከኑዌር ፊትለፊት የተገናኘበት አጋጣሚ ጨዋታውን 2 ለ 0 ቢያደርገው ኖሮ፤ የተለየ ጨዋታ ይሆን ነበር።
በመቀጠል እነሱ አስቆጠሩ ጥራጣሬም ተፈጠረብን፤ ሁለተኛው ጎል ያልተለመደ አይነት ነው ሆኖም ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ስህተት ትሰራለህ ከዛም ትቀጣለህ።
እንዲሮጡ ክፍተት ሰጥተናቸው ነበር፤ አደገኞች ሆነው ተመልክተናል፤ ሆኖም እኛም ሪትሙን ለመጠበቅ ሞክረናል። የተዋሀደ እንቅስቃሴ ብናደረግም ነገሮችን ማፍጠን አልቻልንም፤ ቅያሬዎች ጨዋታው ላይ ለውጥ አርገዋል።"
-ስለ ሳካ አጋጣሚ
" በቫር እንዳዩት እና ፍፁም ቅጣት እንዳልሆነ ነግረውናል።"
ሊሀንድሮ ትሮሳርድ
" ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በመልበሻ ክፍል የተደባለለቀ ስሜት ነው ያለው፤ በመጀመሪያቹ 15 ደቂቃዎች ጥሩ ተጫውተናል፤ እስከ 3 ለ 0 መምራት የሚያስችሉ አጋጣሚዎች ነበሩን፤ ሌላው የነሱን ኳሊቲ በደንብ ተመልከተናል፤ በተለይ ፊትለፊት ላይ ያላቸው ግላዊ ኳሊቲ በጣም ጠንካራ ናቸው፤ መልሶ ማጥቃታቸውም አስፈሪ ነው፤ በዛም ነው የቀጡን፤ አቻ በመውጣታችን ደስተኛ ነን፤ ቀጣዩ ጨዋታ ላይ እኩል እድል ይዘን ወደሜዳ እንገባለን።"
-ስለ ጎሉ
" ጋብሬል ጀሱስ ድሪብል እያደረገ ሳጥን ውስጥ ሲገባ ተመለከትኩት፤ ነፃ ስለነበርኩም ስሙን ጠራሁት፤ ስጠራውም አየኝ እና አቀበለኝ፤ ለኛ ' perfect' ጎል ነው፤ ደስ የሚል ስሜት ሰጥቶናል።"
ሀሪ ኬን
-ስለ ሳካ አጋጣሚ
" 50/50 ነው የእኔ ቡድን ላይ የተፈጠረ ነገር ቢሆን ፍፁም ቅጣት ምቱ ያሰጣል እል ነበር።"
-ስለ ፍፁም ቅጣት ምቱ
" ከፖርቶ ጋር በነበረው የመለያ ምት የራያን የፍፁም ቅጣት ምት አቋም አይቻለው፤ ወድያው ነው ሚወድቀው፤ ስለዚህ አመታቴን በጥቂቱ መቀየር ነበረብኝ፤ ቀድሞ መውደቁ ነገሮችን አቅሎልኛል።"
ቶማስ ቱሄል
" በመጪው ጨዋታ የደጋፊዎቻችንን ብርቱ ድጋፍ እንሻለን፤ ያኔም መሻሻል እንችላለን።"
ኪሚች
" በሜዳችን አርሰናልን ማሸነፍ እንችላለን፤ 2-2 አቻ ማለት ለ0-0 እንደማንጫወት ግልፅ ነው፤ ማሸነፍ አለብን።"
ሪያል ማድሪድ ከ ማንቺስተር ሲቲ
አንቾሎቲ
" የቹያሚኒ ቢጫ? ሚሊታኦ እና ናቾ አሉን፤ ከነሱ አንዱ ይጫወታሉ። ሮድሪጎን በግራ የማጫወቱ እቅድ ሰርቷል። ' fantastic' ውጤት አይደለም ግልፅ ነው ለማሸነፍ ፈልገን ነበር። መጥፎ አጀማመር ነበረን፤ ቀጥሎ ግን በሚገባ ተጫውተናል። ጉልበት ሲጎለን የበለጠ መጥፎ ሆንን፤ ሁለት ምርጥ ጎሎች አስቆጥረዋል። ልናሸንፍም ልንሸነፍም እንችል ነበር፤ በማንቺስተር ተመሳሳይ ጨዋታ መጫወት እንፈልጋለን፤ ምን እንደሚፈጠር እናያለን።"
ሮድሪጎ
" የክሪስትያኖን ቪዲዮዎች ሁሌ አያለሁ፤ አንዳንዴ ከጨዋታ በፊት እመለከታቸዋለሁ፤ ተነሳሽነትም ይሰጡኛል። ጎል ሳስቆጥር አእምሮዬ ላይ ሚመጣልኝ እሱ ነው ስለዚህ እንደእሱ ደስታዬን እገልፃለሁ። ለኔ ጀግናዬ ነው።"
ጋርድዮላ
" ሳንታያጎ በርናቦ ምርጥ ስታድየም ነው፤ የቀራቸው ነገር ሳሩን የተወሰነ ማስተካከል ነው። በሜዳችን ጨዋታውን ማሸነፍ አለብን። ሪያል ማድሪዶች ከባዶች ናቸው፤ በሚገባ ይከላከላሉ ፊት ላይም ሽግግራቸው ፈጣን ነው። የሪያል ማድሪድ ' deflected' ጎል በእድል የተቆጠረ አደለም፤ እኔ በዛ ( በእድል) አላምንም። "
ፌዴ ቫልቨርድ
" በጣም ነው የደከመኝ፤ ሲቲ ኳሱን በሚገባ ተቆጣጥረውታል፤ ነገር ግን ለዚህ ክለብ እስከመጨረሻው ትንፋሼ እሮጣለሁ።"
ግቫርድዮል
" በዚህ ስታድየም ስጫወት የመጀመሪያዬ ነው፤ ድንቅ ከባቢ ነበር፤ በድንቅ ቡድን ላይ የመጀመሪያዬ የማንቺስተር ሲቲ ጎሌን በማስቆጠሬ ደስተኛ ነኝ።"
ፎደን ስለ ጎሉ
" እንደዚህ አይነት ኳሶችን በልምምድ ሜዳ ላይ ሁሌ ነው የምንተግብራቸው፤ የሳጥኑ ጠርዝ ላይ ሆነን እንመታዋለን፤ አንዳንዴ አይገባም፤ ጎሏ ስትቆጠር በማየቴ አመስጋኝ ነኝ።"
የተጠባቂዎቹ ጨዋታዎች ድህረ- ጨዋታ አስተያየት ይህንን ይመስላል።
© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu