Nav And Top Bar

ባለሙያዋ ክሪስትና በአርሰናል የግብ ክልል በእጅ ስለተነካው ኳስ ምን ትላለች?

የእግር ኳስ ህጎች ተንታኝ እና ዳኛ የሆነችው የህግ ባለሙያዋ ' christina unkel' በአርሰናል ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ኳስ በእጅ የተነካችባት አጋጣሚ ፍፁም ቅጣት ምት አያሰጥም ሰትል አስረድታለች።

" ይሄ ፔናሊቲ ነው የምትሉ ከሆነ እግር ኳስን ትጠላላችሁ ማለት ነው" ስትልም ነው ቃልበቃል የተናገረችው ሀሳቧንም ስታስረዳ ህጎች ባለው የጨዋታ ሁኔታ ነው የሚተገበሩት ለዚህም ነው ዳኞች የጨዋታ ህጎች ተግባራዊ ሲያደርጉ ' common sense' እንዲጠቀሙ የሚመከሩት ብላለች ሀሳቧን ስታጠናክርም በዚያን ሰአት በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ የትኛው አጥቂ ነው ጫና ለመፍጠር በሙከራ ላይ የነበረው፤ ሁሉም ቆመዋል ስለዚህ ከባየርሙኒክ የተወሰደ ' advantage' የለም ሰትል ገልፃለች።

አንዲት የCBS ስፖርት ጋዜጠኛም "በህጉ መሰረት የተቃራኒ ቡድን ተጫዋች ጫና ካልፈጠረ እንደዚህ ማድረግ ይቻላል ማለት ነው?" ሰትል የጠየቀቻት ሲሆን ክሪስትናም መለስ አርጋ " እንደዛ ማለት አይደለም፤ ሁኔታውን ማጤን( contextun መረዳት) ይጠይቃል፤ ዳኞች ' common sense 'ን እንድንጠቀም ተፈቅዶልናል፤ ያን አጋጣሚ ከተመለከትን ከባየርሙኒክ የተወሰደ ምንም ' advantage ' የለም ስለዚህ ይሄን ፔናሊቲ ብሎ ቢሰጥ በጨዋታው ላይ ሁሉም ነገር ትክክል አይመጣም ነበር" ብላለች።

IFAB የጨዋታ ህጎችን ተግባራዊ ሲደረጉ ዳኞች ወቅታዊ ሁኔታውን እንዲያጤኑ( common sense ) እንዲጠቀሙ የሚገልፅ ፅሁፍ በ' Laws of the game' በተሰኘው አለም አቀፍ የእግር ኳስ ህጉ መግቢያ ላይ አስቀምጧል።

በአጠቃላይ አጋጣሚው ፔናሊቲ ያሰጣል አያሰጥም ሚለው ነገር ግልፅ የሆነ ማብራሪያ ሊገኝለት ባይችልም ባለሙያዋ ክሪስትና ይሄን አስቀምጣ ለምን እንዳልተሰጠም አብራርታለች።

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu