Nav And Top Bar

ዳኛው ካሜራ አድርገው ወደሜዳ ይገባሉ፤ ለምን?

ዋና ዳኛ ጃረድ ጂሌት ዛሬ ክሪስታል ፓላስ ከ ማንቺስተር ዩናይትድ በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ካሜራ አድርገው ይገባሉ።

ይሄ ካሜራ አድርጎ የመግባት ተግባር በዚህኛው ጨዋታ ላይ ብቻ የሚተገበር ነው።

ለምን?

የእንግሊዝ ኤፍኤ ዳኝነት ምን ይመስላል የሚለውን ለሌሎች ለማሳየት ከቀረፃቸው ኘሮጀክቶች አንዱ ይሄ ነው፤ የሚቀረፀዉ ቪዲዮም ከዳኛ በኩል ጨዋታው እንዴት እንደሚታይ ለማሳየት ይውላል። ኤፍኤውም ክሪስታል ፓላስ እና ማንቺስተር ዩናይትድን ይሄን ኘሮጀክት ጨዋታው ላይ እንዲተገበር ስለፈቀዱ አመስግኗል።

በእንግሊዝ በተለያዩ የሊግ ደረጃዎች በዳኞች ላይ የሚፈፀም የቃላት እና አካላዊ ጥቃት እየተበራከተ መምጣቱ ተገልጿል፤ የተመዘገቡ ጥቃቶችን ብቻ ብንመለከት ካለፈው አመት አንፃር የ1 መቶኛ ጭማሪ አሳይቷል። ለዚህም ነው የተለያዩ ኘሮጀክቶች ተቀርፀው ወደተግባር መገባቱ ያስፈለገው።

ምንጭ: ቢቢሲ እና ስካይ ኒውስ

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu