Nav And Top Bar

50,000 ዶላር በኦሎምፒክ!

የፓሪሱ ኦሎምፒክ ሊካሄድ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተዋል። በየቀኑም በፓሪሱ ኦሎምፒክ ላይ ምን ምን አዳዲስ ነገሮች ልንመለከት እንችላለን የሚሉት ነገሮች ይፋ እየሆኑ ይገኛሉ።

የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ተቋም ባሳለፍነው ወር ይፋ እንዳደረገው ከሆነ ለኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊን የገንዘብ ሽልማት የሚሸልም ፈር-ቀዳጁ የስፖርት ዘርፍ ሆኗል። ከዚህ ቀደም ለኦሎምፒክ አሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት የማይሰጥ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ አለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ከአለም አቀፉ አትሌቲክስ ተቋም ጋር በመተባበር የ50,000 ዶላር ሽልማትን ይዘው መጥተዋል።

በአጠቃላይ 2.4 ሚሊዮን ዶላር ለሽልማቱ ወጪ የሚደረግ ሲሆን ይህም ገንዘብ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ከሚያስገባው ገቢ ላይ ለአለም አቀፍ ስፖርት  ፌዴሬሽኖች በሚያከፋፍለው ገንዘብ  መሰረት ለአለም አቀፉ አትሌቲክስ ተቋም ከሚሰጠው ላይ ወጭ የሚደረግ ይሆናል።

በአትሌቲክስ ስር 48 የትራክ እና የጎዳና( ከትራክ ውጭ) የሚደረጉ ሲሆን በ48ቱም ውድድሮች አንደኛ ሆነው የሚወጡት አትሌቶች ከሚያገኙት የወርቅ ሜዳሊያ በተጨማሪ 50,000 የአሜሪካን ዶላር ሽልማት ይበረከትላቸዋል።

የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ተቋም ኘሬዝዳንት ሰባስትያን ኮ " ለኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት መሰጠት መጀመሩ ለተቋሙ እና ለአትሌቲክስ ስፖርቱ በአጠቃላይ ትልቅ እመርታ ነው" ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ግዙፉን ሀገርን ወክሎ ለማፋለም የሚደረገውን የኦሎምፒክ ውድድር ከገንዘብ ጋር ማያያዙ
የማይቻል ቢሆንም በአትሌቶቻችን አማካኝነት ከሚገኘው ገቢ እነሱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።


በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዎች ተርታ የሚጠቀሰው አትሌት ሀይሌ ገ/ ስላሴ በሸገር ስፖርት የተጠየቀ ሲሆን ሽልማቱ በጎም መጥፎም ጎን አለው ማለት ይቻላል፤ አትሌቶችን ማበረታተቱ ተገቢ ሆኖ ሳለ በሀገራዊ ስሜት ላይ ጥላ እንዳያጠላ መደረግ ይኖርበታል ብሏል።

አለምአቀፉ የኦሎምፒክ ተቋም 90 መቶኛ የሚሆነውን ገቢውን ለሀገር አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴዎች እና ለየሀገራቱ ስፖርት ፌዴሬሽኖች ያጋራል።

የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከቀጣዩ ኦሎምፒክ ጀምሮ ደግሞ ሽልማቱን ለብር እና ነሀስ አሸናፊዎችም ለማስፋት እየሰራ እንዳለ ገልጿል።

የፓሪሱ ኦሎምፒክ  እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር ሀምሌ 26,2024 የሚጀምር ሲሆን በነሀሴ 11,2024 የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ዘገባውን ለማጠናቀር አለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሚዲያ አውታሮችን እንደዋቢ ተጠቅመናል።

ግንቦት 9,2016 አ.ም

SKY ስፖርት ET™

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu