ከባለቤቴ ጋር የተዋወቅንበትን አጋጣሚ ለራሷ ራሱ ነግሬያት ማውቅ አይመስለኝም፤ ባልናገር እመርጣለሁ፤ ግን ያው እውነት እንደምናገር ቃል ስለገባሁላችሁ፤ መናገር እንዳለብኝ አስባለሁ።
ከባለቤቴ ጋር ትውውቃችን የጀመረው በአንድ ትዊት ነው። በውሰት በወርደር ብሬመን ሳለሁ ጥቂት ሺህ ተከታዎች ነበር የነበሩኝ፤ የሆነ ቀን ስለጨዋታ አልያም ሌላ ነገር ፤ብቻ ስለምን እንደነበር ትዝ አይለኝም ትዊት አደረኩ። ይህቺ ውብ ሴትም ላይክ አደረገችው፤ ጓደኛዬም ያንን አየ። በዛን ወቅት ' single' ነበርኩ። ጓደኛዬ " በጣም ታምራለች አይደል? ሚሴጅ ላክላት" አለኝ።
እኔ " አይሆንም፤ ሰዎች እኔን አይወዱኝም፤ ቴክስቴን አትመልስም" ስል መለስኩለት።
ቀጥሎ ስልኬን ተቀበለኝና ለሷ ሚሴጅ መፃፍ ጀመረ፤ የፃፈውን ሚሴጅ እያሳየኝም " ልላከው ወይ" ይለኝ ጀመር። እኔ አፍሬ መሬት ላይ ተዘርሬ ነበር ነገር ግን ምክንያቱን መግለፅ ባልችልም " አዎ ላከው" አልኩት።
ሚሴጁን ከላከላት በኋላም መልሳ ፃፈችልኝ። በቴክስትም ለተወሰኑ ወራት አወራን። እኔ አንድን ሰው ከተዋወኩ በኋላ ነገሮችን ለመቀጠል አይከብደኝም። ደስ የሚል ነገር ነበር። ህይወቴን በብዙ መልኩ ቀይራዋለች። እሷ ባትኖረኝ ምን ማድረግ እንደምችል ራሱ አላውቅም።
ባለቤቴ የህይወቴ ወሳኟ ሰው ናት። እኔ ህልሜን እንድከተል ብላ ብዙ ነገር መስዋእት አድርጋ በ19 አመቷ አብራኝ ተጉዛለች። ከሰዎች ጋር የተሻለ ግንኙነት እንዲኖረኝ እና ለውጤታማነቴ ረድታኛለች። ሁሉን ነገሬን በአስገራሚ ሁኔታ ተቆጣጥራዋለች።
በ2015 የዝውውር ጊዜ ወቅት ባለቤቴ የመጀመሪያ ልጃችንን አረገዘች። በወቅቱ ማንቺስተር ሲቲ፣ ፒኤስጂ እና ባየርሙኒክ እኔን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተው ነበር። አስጨናቂ ወቅት ነው። ገና ቤተሰብ መመስረቴ ነው እና ደግሞ ማረፊያዬ የት እንደሆነ በውል አልታወቀም።
በግሌ ሲቲ ለመግባት ነበር የፈለኩት። ኮምፓኒ ቴክስት ያረግልኝ የነበረ ሲሆን ስለኘሮጀክቱ እየነገረኝ ብመጣ እንደምወደው ይገልፅልኛል። ስለክለቡ ጥሩ ስሜት ነበረኝ፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ግን ወልፍስበርግን ክብር መንሳት አልፈለኩም፤ በዛ የነበረኝን ጊዜ እወደዋለሁ። ስለዚህ ዝም ብዬ ሚሆነውን መጠባበቅ ያዝኩ።
በየቀኑ ለተከታታይ 3 ሳምንታት ወኪሌ " ሊሳካ ነው፤ አልተሳካም፤ ሊሳካ ነው፤ አልተሳካም..." ነበር ወሬው። ይሄ ጭንቀት ባለቤቴ ላይም ተፅእኖ አሳድሯል። ከእለታት አንድ ቀን ጠዋት ስንነሳ በጣም አመማት። ምን ማድረግ እንዳለብን ግራ ገባን። ከፅንሱ ጋር በተገናኘ የሆነ ችግር ይኖር ይሆን ወይ ብለን ሰጋን።
በጣም አሟት ነበር፤ በተጨማሪም ደም ይፈሳት ጀመር። ምን እየሆነ እንዳለ አናውቅም፤ በቀጥታ ወደሆስፒታል ገሰገስን። ፅንሱን እናጣው ይሆን ወይ ብለን ፈራን። ምንም ጥያቄ የለውም የህይወቴ አስቀያሚው ጊዜ ነው።
እግዚአብሔር ይመስገን፤ በስተመጨረሻ ሁሉም ነገር ሰላም ሆነ፤ ፅንሱም ደህና ሆነ።
በእግር ኳስ ያገኛኋቸው ነገሮች ሁሉ ከባለቤቴ እና ከልጆቼ አይበልጡም። ያ ወቅት ህይወቴን ከቀየሩ አጋጣሚዎች አንዱ ነው፤ እግር ኳስ የህይወት ወይም የሞት ጉዳይ አለመሆኑን ያየሁበት፤ ይመስለኛል የመጀመሪያዎቹ 23 አመታት የህይወቴን ክፍል በእግር ኳስ በጣም ተስቤ ነው ያሳለፍኩት፤ ነገር ግን ባለቤቴን ካገኘሁ በኋላ በተለይም ደግሞ የመጀመሪያ ወንድ ልጃችን ከተወለደ በኋላ ሁኔታው ተቀየረ፤ ወደእንግሊዝ ከሄድኩ እና ለሲቲ መጫወት ስጀምር ሁሉም ነገር ጀመረ፤ በተለይም ፔፕ በሁለተኛ የውድድር ዘመኔ ከመጣ በኋላ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ሄዱ።
ፔፕ እና እኔ አንድ አይነት ' ሜንታሊቲን' እንጋራለን። ከኔ ይልቅ እሱ በእግር ኳስ ፍቅር እጅጉን ተለክፏል። ሁሌ እንደተጨነቀ ነው። በኛ በተጫዋቾች ላይም ጭንቀት አለ ግን እሱ ከኛ በእጥፍ ሚጨነቅ ይመስለኛል፤ ምክንያቱም ማሸነፍ ብቻ አይደለም ሚፈልገው ' ፍፁማዊነትን' ጭምር እንጂ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ፔፕን ሳገኘው ቁጭ አድርጎኝ " ኬቨን አንተ በቀላሉ ከአለማችን አምሰት ምርጥ ተጫዋቾች አንዱ ትሆናለህ" አለኝ። እኔ ተገርሜያለሁ፤ ግን ፔፕ በጠንካራ እምነት ነበር ያንን የተናገረው። እናም ትክክል እንደሆነ ማሳየት አለብኝ ስል ቆረጥኩ።
ብዙውን ጊዜ እግር ኳስ ከ' ኔጋቲቪቲ' እና ፍርሀት ጋር የተያያዘ ነው፤ ፔፕ ጋር ግን ከፍተኛ ' ፖዘቲቪቲ' አለ። ግቡን( መድረስ ሚፈልግበትን ደረጃ) ከፍ አድርጎ ይሰቅለዋል። አዎ ታክቲካል ማስተር ነው፤ ግን ሰዎች ማያዩት ' ፍፁም' ለመሆን ምን ያህል ጫና ራሱ ላይ እንደሚያሳርፍ ነው።
ኬቨን ዴብርያን - " እንዳወራ ፍቀዱልኝ"
የካቲት 13, 2016 አ.ም
SKY ስፖርት ET™
© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu