Nav And Top Bar

"የተላለፈብኝ እገዳ የተጋነነ ነው "- ዳኛ ጃን ስሚት

ዋንጫውን ካሸነፈው ክለብ ጋር አብሮ ሲጨፍር የታየው ይህ ዳኛ የተላለፈብኝ እገዳ የተጋነነ ነው ብሏል።
የሚወደውን ክለብ ለመጥቀም በሚል ሶስት ተጫዋቾችን በቀይ ካርድ ያስወጣው ዳኛ የእድሜ ልክ እገዳ እንደተጣለበት ይታወሳል።

ጃን ስሚት የአውሮፓዊቷ ሆላንድ ዜጋ ሲሆን ህይወቱን የእግር ኳስ ጨዋታዎችን በመዳኘት ይመራል።
ከሁለት ሳምንት በፊት በአራተኛው የሆላንድ ሊግ የዋንጫ ጨዋታን እንዲዳኝ የተሰየመው ይህ ዳኛ በእግር ኳስ ላይ ግፍ ፈጽሟል ተብሏል።

በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኤስቪ ዲ ቫልክልን እግር ኳስ ክለቦች መካከል የተካሄደው ይህ የዋንጫ ውድድር አሸናፊው ክለብ ወደ ሶስተኛ ዲቪዚዮን የማድግ እድልም በመያዙም ፉክክሩ ከባድ እንደነበር ተገልጿል።

ይህ ዳኛም የቅዱ ጊዮርጊስ ክለብ ደጋፊ ነበር የተባለ ሲሆን የሚደግፈው ክለብ ወደ ሶስተኛ ዲቪዚዮን እንዲያድግ እና ዋንጫ እንዲበላ በሚል ሶስት የተቃራኒ ክለብ ተጫዋቾችን በቀይ ካርድ ማሰናበቱን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።

ከዚህ በተጨማሪም ይህ ዳኛ ከጨዋታው አሸናፊ ክለብ ጋር በመሆን ሲጨፍር እና ዋንጫውን አንስቶ ደስታውን ሲጋራ የሚያሳዩ ምስሎች ተሰራጭተዋል።
ይህን ተከትሎም ግፍ ተፈጽሞብኛል ያለው ክለብ ለውድድሩ አዘጋጅ አካል ክስ ያቀረበ ሲሆን የሀገሪቱ እግር ኳስ አወዳዳሪ አካል ዳኛው እግር ኳስ ጨዋታዎችን እንዳይዳኝ የእድሜ ልክ ቅጣት ጥሏል።
ቅጣት የተጣለበት ዳኛም "እኔ የተጫዋቾቹን ደስታ ነው የተጋራሁት፣ አንድ ጊዜ ብቻ ዋንጫውን አንስቻለሁ፣ ተጫዋቾቹንም እንኳን ደስ አላችሁ ብያለሁ ከዚህ ውጪ ያደረስኩት ጥፋት የለም የተወሰደብኝም ቅጣት የተጋነነ ነው" ሲል ተናግሯል።

አልአይን እንደዘገው

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu