Nav And Top Bar

ፒንክ ካርድ ትግበራ ላይ ሊውል ነው!

በመጪው ኮፓ አሜሪካ ፒንክ ካርድን ተግባራዊ ሊያደረግ መወሰኑን የደቡብ አሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ' CONEMBOL' አስታውቋል። 

ተቋሙ ፒንክ ካርድ እንዴት አገልግሎት ላይ እንደሚውል
ሲያብራራም ግጭት ( Concussion ) ያጋጠማቸው ተጫዋቾች ጨዋታውን የማያስቀጥል ሁኔታ ውስጥ የመግባት እድላቸው ሰፊ ስለሆነ እነሱ ሊቀየሩ ሲሉ ዳኛው ፒንክ ካርድ ያሳያል ይሄም ማለት ቡድኑ የተጎዳውን ተጫዋች ሲቀይር ከተፈቀደለት አምስቱ ቅያሬ ጋር አይቆጠርም፤ በጨዋታው ላይ ገና ያልተነካ 5 ቅያሬዎች አሉት ማለት ነው።

ይሄንን ለማካካስ ደግሞ ተቃራኒ ቡድን ከ5ቱ ቅያሬ በተጨማሪ አንድ ተጫዋች ጨምሮ የመቀየር እድል ይሰጠዋል። በአንድ ጨዋታም አንድ ቡድን ሊያገኝ የሚችለው ፒንክ ካርድ ከአንድ የማይበልጥ ይሆናል።

በአጠቃላይ አንድ ተጫዋች በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ' consciousness'ን የሚያጣ ከሆነ (suspected cranioencephalic trauma and concussion) በሱ ምትክ የሚቀይረው ተጫዋች ካሉት አምስቱ ተቀያሪዎች 4 ቅያሬ ብቻ እንዲቀረው አያደርግም፤ ከአምስቱ ላይ አይነካም። ለተቃራኒ ቡድን ደግሞ ከአምስቱ በተጨማሪ አንድ ተጫዋች ጨምሮ መቀየር ይፈቀድለታል።

' consciousness'ን እንዳጣ የተገመተ ተጫዋች ለህክምና ከሜዳ ከወጣ በኋላ ተመልሶ መግባት አይችልም። የደቡብ አሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም በእንደዚህ አይነት ያልታሰበ ቅያሬ ቡድኖች የሚደረስባቸውን ጉዳት ለመቀነስ እንደዚህ አይነት ህግ ተግባር ላይ ለማዋል ወስኗል።

የካቲት 15,2016

SKY ስፖርት ET™

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu