Nav And Top Bar

"ይሄ ህልምህ ነው መጓዝህን ቀጥል" ያልሽኝን አስታውሺ...

ከአራት አመታት በፊት እዚህ ለመምጣት እድሉን ሳገኝ የት እንደነበርኩ አልረሳውም። በመኝታ ቤት አነስተኛ ክፍል ውስጥ ቆሜ ነበር። ወኪሌ ማታ 4:00 አካባቢ ደወለ ፤ በዚያንጊዜ ሴት ልጄ ገና 3 አመቷ ነበር፤ ለዛም ሰአቱ ለኛ የእንቅልፍ ሰአት ነው። እሷን አንዳልረብሻት ብዬ ከአልጋ ላይ ወረድኩና ወደአነስተኛ ልብስ ማስቀመጫ ክፍል ጋር አመራሁ፤ በእግር ኳስ ዘመኔ ሁሉ ወኪሌን " 100% እውነታ ያልሆነ ነገር ከሆነ ስለዝውውር መስማት አልፈልግም እለው ነበር፤ እውነተኛ ፍላጎት ካልቀረበ በቀር መረበሽ( ሲላላ) አልፈልግም።

ስለዚህ በዚያ ሰአት ሲደውልልኝ የሆነ ነገር እየተካሄደ እንደሆነ አውቄያለሁ።

የልብስ ማስቀመጫውን ክፍል በር ዘጋሁና " ሄሎ ሚጉዌል" አልኩት፤ እሱም " ዜናውን ለመስማት ዝግጁ ነህ?" አለኝ፤ እኔም " ስለ ምን" አልኩት ። " ስለመሄድ" ሲል መለሰለኝ እኔም " የት ስለመሄድ? ወደ ስፐርስ( ቶተንሀም) ነው?" ስል መለስኩለት። " ዩናይትድ" አለ መልሶ፤ " እየቀለድክ ነው" ስለው ጊዜ " አይደለም፤ የምሬን ነው፤ ዩናይትድ፤ አልቋል፤ አሁን ያንተ ውሳኔ ነው ሚጠበቀው፤ ምንድነው ፍላጎትህ" አለኝ። መልስ አልሰጠሁትም፤ እምባዬን ለመቆጣጠር ስሞክር ነበር፤ እምባችሁን ለመቆጣጠር ስትሞክሩና ሌላኛው ሰው ለቅሷችሁን እየታገላችሁ እንደሆነ ሳይገባው ወሬውን ሲቀጥል እናንተ ማውራት ሲያቅታችሁ ያለውን ስሜት ታቁታላቹ አይደል፤ እሱ " ቡርኖ ቡርኖ ሄሎ" ይላል፤ በዚያን ጊዜም አና( ባለቤቴ) መኝታ ቤት መታ አልጋ ላይ ስታጣኝ " ቡርኖ ቡርኖ" እያለች መጣራት ጀመረች፤ የልብስ ማስቀመጫውን ክፍል በር ስትከፍተውም አገኘችኝ፤ " ምን እየተካሄደ ነው፤ ለምንድነው የልብስ ማስቀመጫ ውስጥ ያለሀው" አለችኝ።

እኔም " ሚጉዌል ነው የደወለው፤ ዩናይትድ እንደሚፈልገኝ ነገረኝ" አልኳት። እሷም " ምን?....እያለቀስክ ነው?" አለችኝ። " አላውቅም፤ የደስታ ይመስለኛል" ስል መለስኩ፤ አና በፍፁም አታለቅስም፤ ጠንካራ ነች፤ እኔ ደሞ ቶሎ ስሜታዊ ሚሆን ሰው ነገር ነኝ፤ ይሄንን ስታነበውም እንደምትስቅብኝ አውቃለሁ።

የነበርኩበትን ሁኔታ በተወሰነ መልኩ መረዳት ይኖርባችኋል። ባለፈው ክረምት( ዩናይትድ ከመግባቴ በፊት) የኘሪምየር ሊግ ክለቦች እንደፈለጉኝ የሚገልፁ አንዳንድ ጭምጭምታዎች ነበሩ፤ ግን እውነተኛ እና ገፋ ብሎ የመጣው ጥያቄ የቶተንሀም ነበር። አሁን ለኔ ' weird' ስሜት ነው ሚሰማኝ በወቅቱ የነበረኝ ነገር ግን በጥያቄው ተደስቻለሁ። ከህይወቴ አላማዎች አንዱ የነበረው በኘሪምየር ሊግ መጫወት ነው። ምንም አይነት ወሬዎችን ለመገደብ ፈለኩ፤ ግን በሶሻል ሚዲያ ዘመን ይሄ አስቸጋሪ ነው፤ ጓደኞቼ ዜናዎቹን ይነግሩኛል ። በመጨረሻ ግን ክለቦቹ ሳይስማሙ ቀሩ፤ ዝውውሩም ሳይሳካ ቀረ። የተደበላለቀ ስሜት ነው የሰማኝ፤ ግን በስፖርቲንግ ደስተኛ ነበርኩ፤ የደጋፊዎቹን ፍቅር ወድጄዋለሁ እናም ለኔ ምርጥ ቦታ ነበር፤ ሆኖም የመጨረሻ ማረፊያዬ እዛ አይደለም።

ከጥቂት ወራት በኋላ አዲሱ የውድድር ዘመን ተጀመረ፤ እኔም ሁሉንም ወሬዎች ለመገደብ ሞከርኩ። ታዲያ ወኪሌ በጥር ደውሎ " አይደለም የምሬን ነው፤ ዩናይትድ፤ ምንድነው ውሳኔህ" ሲለኝ ደንግጫለሁ።

ለአናም " በስፖርቲንግ ህልሜን እየኖርኩ እንዳለሁ ይሰማኛል፤ ግን ይሄ ከህልምም በላይ ነው፤ ማንቺስተር ዩናይትድ እኮ ነው" ነበር ያልኳት። ይሄ ሁሉ ሲሆን ከወኪሌ ጋር የነበረኝ የስልክ ግንኙነት አልተቋረጠም፤ ' hold' አርጌው እንደነበር ራሱ አላስታውስም፤ ምናልባትም ስለስምምነቱ እያወራ እና እኔም መልስ እያልሰጠሁት ይሆናል፤ በመጨረሻም " ሚጊዌል" አልኩት። እሱም " አቤት" ሲል መለሰ፤ መልሼም " በቃ ወደዩናይትድ እንሄዳለን" አልኩት። ስልኩን ዘግቼም ባለቤቴን አቅፌያት የደስታ እምባ አነባሁ።

አና ከ16 አመቴ ጀምሮ በኔ ህይወት ውስጥ ነበረች፤ ገና አፍላ ወጣት ሳለን ተገናኘን፤ ልክ የፍቅር ህይወት ስንጀምር እኔ እንደ እግር ኳስ ተጫዋችነቴ ገንዘብ እየሰራሁ አልነበረም። እሷ ደግሞ ቅዳሜ ቅዳሜ የፉትሳል ዳኛ ሆና እያገለገለች ገንዘብ ይከፈላት ነበር። በተከታታይም ከ3-4 ጨዋታዎች ታጫወታለች። እሁድ እሁድ ደግሞ ሲኒማ እንሄዳለን። በወቅቱ ያን ያህል ገንዘብ አልነበረኝም፤ ስለዚህ ለፊልም ትኬት ምትከፍለው አና ነበረች። ራት ስንወጣም እንደዛው፤ ፒዛ ቤት ራሱ እሷ ነበረች ምትከፍለው። በ17 አመቴ ጣልያን ስሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ በልምምድ ማእከል መኖር ጀመርኩ። በ18 አመቴ እሷ ሀይስኩል ጨረሰች እናም ተከተለችኝ። ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ይሄን ህልም አብረን ነው የተጓዝነው።

ስለዚህ የደስታ እምባ ሳነባ፤ ባለን ታሪክ የተነሳ ነው።

(አና ይሄ ላንቺ ነው...አስታውሺ በቡድን ራት ላይ ሆነን የዩዲኒዜ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ደውሎ ከዚህ በኋላ አንፈልግህም ሲለኝ ራቱን ትቼ በሆቴል ሳለቅስ አስታውሺ፤ አስታውሺ ያልሽኝን፤ ይሄ ህልምህ ነው መጓዝህን ቀጥል ነበር ያልሽኝ።)

አሁን የት እንዳለን ተመልከቱ...እነዛ ከባድ ጊዜያት አልሰበሩንም።


ቡርኖ ፈርናንዴዝ- ከውድ ዩናይትድ የተቀነጨበ

የካቲት 18,2016 አ.ም

SKY ስፖርት ET™

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu