Nav And Top Bar

"ከምንም በላይ ዲሲፕሊን"

ማሬስካ ማናቸው?

ማሬስካ ማንቺስተር ሲቲ የሶስትዮሽ ዋንጫን እንዲያሳካ ከፔፕ ጋርድዮላ ስር በመሆን በረዳት አሰልጣኝነት ጥሩ ሚናን ከተወጣ በኋላ ወደ ሻምፒዮንሺፑ የወረደውን ሌስተር ወደላይ የማሳደግ ጫና ጫንቃው ላይ እንዲያርፍ የሚያደርገውን የሌስተር ሲቲ ስራን ለመረከብ ደፈረ።

ማሬስካ ሌስተርን ከመያዙ በፊት ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ጨዋታ የመራው በአንድ አጋጣሚ ሲሆን እሱም በፓርማ እያለ 14 ጨዋታዎችን ብቻ የመራበት አጋጣሚ ይጠቀሳል። ፓርማ ከሴሬኣ ከወረዱ በኋላ ወደሴሬኣ የመመለስን አላማ ሲሰንቁ ማሬስካን ቀጠሩ ሆኖም ውጤታቸው አለማረምና ከ6 ወር በኋላ ተሰናበቱ።

የቼልሲ ደጋፊዎች የማሬስካን በዋና አሰልጣኝነት ዘለግ ያለ ልምድ ያለመኖር ስጋት ውስጥ ሊከታቸው ይችላል፤ ቢከታቸውም ትክክል ናቸው። ሆኖም የማይካድ አንድ ሀቅ አለ ማሬስካ ለስራቸው እጅግ የተሰጡ እና ለድል የተራቡ አሰልጣኝ መሆናቸውን በቅርብ ሚያውቋቸው ሁሉ ይመሰክራሉ።

በፔፕ ስር ሰርቶ የሶስትዮሽ ዋንጫን ካሳካ በኋላ ወደ ሌስተር ያቀናው ማሬስካ ሌስተር ከሊጉ በወረደበት አመት ያደረጋቸውን እያንዳንዱን ጨዋታዎች በጥልቀት ተመልክቷቸዋል፤ አንዳንዶቹን ከአንዴ በላይ እንዳያቸው ይነገራል። ለእያንዳንዱ ጨዋታ ሲዘጋጅም የተቃራኒ ቡድን ቪዲዮዎችን ለሰአታት ይመለከታል፤ አጨዋዋታቸውንም በሚገባ ያጠናል።

ማሬስካ ታክቲካል አሰልጣኝ ነው፤ የሌስተር ተጫዋቾች ዘንድሮ የሰሩት የአካል ብቃት ልምምድ ከሌላው ጊዜ የተለየ አይደለም፤ የሰውዬው ትኩረት የነበረው ታክቲክ ነው። በሲግሬቭ የልምምድ ማእከል ሜዳ ላይ በቀን ሁለቴ ልምምድ የሚያሰራቸው ሲሆን በክፍል ውስጥ ደግሞ የቪዲዮ ትንታኔን ይሰጣል።

አሰልጣኙ ለስራው የተሰጠ እንደሆነ ሚያስታውቀው ወደክለቡ ከተዘዋወረ በኋላ የቅድመ- ውድድር ዘመን ዝግጅት ወቅቱን በሲግሬቭ የልምምድ ማእከል ማሳለፉ ነው፤ ምንም እንኳን ሌስተሮች ቤት ቢያመቻቹለትም እርሱ ግን ራሱን ከክለቡ ጋር ለማዋሀድ በማሰብ ማረፊያውን በሲግሬቭ የልምምድ ማእከል ነበር ያደረገው። ምሽቱን ደግሞ ወጣ ብሎ ከማሳለፍ ይልቅ የቡድኑን ያለፉ ጨዋታዎች ተንቀሳቃሽ ምሰሎች( ቪዲዮዎች) መመልከት ያዘወትራል።

ማሬስካ ቡድኑን ይዞ ለቅድመ-ውድድር ዘመን ዝግጅት ወደሌላ ስፍራ ከማቅናት ይልቅ ለሳምንት ከሱ ጋር እንዲቆዩ አድርጓቸው የሱን የእግር ኳስ ፅንሰ-ሀሳብ እንዲረዱ ለማድረግ ሞክሯል።

አሰልጣኙ ታክቲክን ሲያስረዳ ቀለል ባለ መልኩ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ። የሌስተሩ ተጫዋች kiernan Dewsbury-Hall ለመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ተጫዋቾች በሱ አዲስ የታክቲክ ማስረዳት ስታይል ተጫዋቾች ግራ እንደተጋቡ ያስታውሳል፤ "እሱ ነገሮችን የሚያስረዳበቶ መንገድ፤ ነገሮቹን ቀላል አድርጓቸዋል፤ ' እንዴት ይሄን ሳናውቀው ልንቀር ቻልን' አስብሎናል" ሲል ይናገራል።

አሰልጣኙ ምንም አይነት የተጫዋች ኢጎ ማስታመም ሚባል እርሱ ጋር የለም፤ ቼልሲ ሲመጣም ወዲያውኑ ማን ከእርሱ ጋር ይቀጥላል፤ ማንስ አይቀጥልም የሚለው ላይ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል። " የማልታገሰው ነገር መጥፎ ባህርይን ወይም ለእኔ፣ ለስታፎች እና ለቡድን ጓደኞቹ ክብርን የማይሰጥ ተጫዋችን ነው" ሲል ነበር ለዘአትሌቲክ በአንድ ኢንተርቪው ላይ የገለፀው።

አሰልጣኙ እንደየጨዋታው ተቀያያሪ የጨዋታ ዘይቤን ወደሜዳ ይዞ ቢገባም በሱ ቡድን ሊቀሩ የማይችሉ ነገሮች አሉ: እነርሱም አንድ አጥቂ፣ አንድ ነጣቂ አማካይ( DMF)፣ በጥልቀት የሚጫወት ፉልባክ እና ሁለት የክንፍ ተጫዋቾች ናቸው።

በኘሪምየር ሊጉ ይሳካለታል ወይ የሚለውን ጊዜ የሚፈታው ጉዳይ ይሆናል።

ዘ አትሌቲክ እንደዘገበው

የካቲት 19,2016 አ.ም

SKY ስፖርት ET™

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu