ካካ ማልፔንሳ ኤርፖርት ሲደርስ እጆቼን ራሴ ላይ ጫንኩ። መነፅር አድርጓል፤ ፀጉሩ በሚገባ የተበጠረ ነው፤ የሆነ አለ አይደል መልካም ፀባይ ያለው ልጅ ይመስላል።
የቀረው ነገር ቢኖር ደብተር እና ስናክ ነው እንጂ በቃ ቁጭ የኮሌጅ ተማሪ ነው ሚመስለው። ምንም ብራዚላዊ ሚያስመስለው ነገር የለም። የጆቫ ዊትነስ ተከታይ ነው ሚመስለው።
በመጀመሪያው የሚላን ትሬኒንግ ወቅት ከጋቱሶ ፊትለፊት ተጋፈጠ፤ በትከሻውም መታ አድርጎ ሊያስቆመው ሞከረ እርሱ ግን ኳሷን እንደያዛት 30 ያርድ ርቀት ላይ ለሚገኝ የቡድን አጋሩ አቀበለው። ኳስ ሲይዝ የሚያደርጋቸው ነገሮች በሙሉ አስደናቂ ናቸው። እኔ የሆነ ሰአት ላይ ተደንቄ ቃላት አጥሮኝ ነበር። የማያቸውን ነገሮች ቃላት አይገልፁልኝም።
በእርግጥም ይህ የጆቫ ዊትነስ ተከታይ የመሰለ ልጅ ከፈጣሪ ጋር በቀጥታ የሚያወራ ነው፤ እርግጠኛ ነኝ በአንዱ ግንኙነታቸው ስለእግር ኳስ አውርተዋል።
ሁሌ ልምምድ ካበቃ በኋላ እኔ እና ጋላኒ ( የቀድሞ የኤሲ ሚላን ዋና ስራ አስፈፃሚ) እናወራለን፤ እናም ሀሳቡን ለመስማት ምን እየተካሄደ እንዳለ እነግረዋለሁ።
ካካን ለመጀመሪያ ጊዜ የልምምድ ሜዳ ላይ ያየሁበት እለት ደወልኩለትና " አንድ ዜና አለኝ" አልኩት፤ " ጥሩ ወይስ መጥፎ" አለ መልሶ ጋላኒ፤ እኔም " ጥሩ፤ በጣም ጥሩ" አልኩት፤ " ካሪሊቶ መልቀቂያ ልታስገባ ነው እንዴ?" አለኝ፤ " አይደለም እቆያለሁ ምክንያቱም ድንቅ ሰው አስፈርመናልና" ስል መለስኩለት።
አንቾሎቲ በሚላን ካካን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዩበትን ቀን እንዲህ ያስታውሳሉ።
ግንቦት 20,2016 አ.ም
SKY ስፖርት ET™
© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu