Nav And Top Bar

" ምህረት የለሽ መሆን እንዳለብኝ ገና በአፍላ ወጣትነት እድሜዬ ተረድቻለሁ"

ልክ ታዋቂ ሰው ስትሆን ሰዎች በሆነ መንገድ ' act' እንድታደርግ ይጠብቃሉ። ልክ ሁሉን ነገር ማድረግ እንደሚችል ሱፐር ሂሮ የሆንክ ይመስል። ኳስ መጫወት ትችላለህ፤ ስለዚህ በደንብ መናገር እንድትችል እና በራስ መተማመንህ የላቀ እንዲሆን ይጠበቃል፤ ሆኖም ይሄ መሬት ላይ ያለ እውነታ አይደለም።

ይመስለኛል አፍላ ወጣት ሆኜ ለማድሪድ ስፈርም የሰጠሁት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰዎች በምን ውስጥ እያለፍኩ እንዳለሁ እንዲረዱ አድርጓል።

ማድሪድ ገብቼ በይፋ ከተዋወኩ ከጥቂት ቀናት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ልምምድ ማእከል ሄድኩ፤ መኪና ለመንዳት እድሜዬ ስላልደረሰ አባቴ ከኢስኮ፣ ሮናልዶ፣ ራሞስ፣ ሞድሪች እና ቤንዜማ የመሳሰሉ ተጫዋቾች ጋር እንድጫወት ማድረስ ነበረበት፤ ልክ ትምህርት ቤት ሚያደርሰኝ ይመስል።

እኔ እያሰብኩ የነበረው ስፓኒሽ ማውራት ለማልችለው ለኔ ትንሹ ልጅ እነዚህን የመሳሰሉ ክዋክብት በመልበሻ ክፍል ለኔ ምን አይነት ቦታ ይሰጡኛል የሚለውን ነበር፤ ነገር ግን ሁሉም ቀና ነበሩ፤ እንግሊዘኛ መናገር የሚችሉት እንደ ክሩስ፣ ሞድሪች እና ሮናልዶ ያሉት ተጫዋቾች የብቸኝነት ስሜት እንዳይሰማኝ ተንከባክበውኛል። ከተሞክሯቸው ተነስተው ምክርም ሰጥተውኝ ነበር፤ ይሄም እጅግ በጣም ረድቶኛል፤ ግን እውነቱን ለመናገር የትኛውም የቡድኑ ተጫዋች አንድ 16 አመት ኖርዌጂያን ቦታዬን ይቀማኛል ብሎ አላሰበም።

ከክለቡ ጋር አንድ እቅድ አወጣን፤ ይህም ሁሌ ከዋናው ቡድን ጋር ልምምድ እሰራለሁ፤ ከዛም በ' B' ቡድኑ ደግሞ ወጥ የሆነ የጨዋታ ጊዜ አገኛለሁ የሚል ነበር። በወቅቱ ምርጥ እቅድ ቢመስልም ኋላ ላይ ግን ከሁለቱም ሳልሆን እንድቀር አድርጎኛል።

ከ'B' ቡድኑ ጋር በወጥነት አብሬያቸው ስላልሆንኩ ትስስሩን ላገኘው አልቻልኩም። በዋናው ቡድን ደግሞ ልምምድ ለመስራት የሚመጣ አንድ ' ታዳጊ' ነበርኩ፤ በጨዋታዎች አልሳተፍም፤ እናም በሁለቱ መሀል አጣብቂኝ ውስጥ ገባሁ።

በወቅቱ ኳስን ከመጫወት ይልቅ እሰጋ የነበረው ስህተቶችን ላለመስራት ነበር። አጨዋወቴም ሁሌ ተፅእኖ መፍጠርን ያለመ ሲሆን አስቸጋሪ ኳሶችን ማቀበልን ያካትታል። አሁን የምታዩት አጨዋወቴ ከዛን ጊዜ ጀምሮ የተሰራ ነው፤ ገና አፍላ ወጣት ነበርኩ ግን ምህረት የለሽ መሆን እንደሚገባ ተረድቻለሁ። እውነተኛው አንተነትህን በሜዳ ላይ ማሳየት ይኖርብሀል።

ማርቲን ኦዴጋርድ- ከምንጊዜም ሰሜን ለንደን የተቀነጨበ

ግንቦት 21,2016 አ.ም

SKY ስፖርት ET™

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu