Nav And Top Bar

ቫር በሊጉ የመቀጠሉ ነገር ዛሬ ውሳኔ ያገኛል!

ቫር ከሊጉ ይወገድ የሚለው ኘሮፖዛል ላይ ዛሬ ድምፅ ይሰጣል። ቫር ከሊጉ ይወገድ የሚለው ይህ ኘሮፖዛል ድምፅ የሚሰጥበት ዛሬ የሊጎቹ ጠቅላላ ጉባኤ በሚካሄድበት ወቅት ነው። ቫር በእንግሊዝ ኘሪምየር ሊግ መተግበር ከጀመረ አንስቶ ብዙ አወዛጋቢ ነገሮች ማስነሳቱ ይታወሳል።

በወርሀ ግንቦት መጀመሪያ አካባቢ ወልቭስ ለሊጉ ቫር ከሊጉ ይወገድ የሚል ኘሮፖዛል ማስገባቱ ይታወሳል። የትኛውም የሊጉ ክለብ በሊጉ የሚተገበሩ ነገሮች ላይ ማሻሻያዎች እንዲኖሩ ኘሮፖዛል ማስገባት የሚችል ሲሆን፤ ያ ኘሮፖዛል ተቀባይነት የሚያገኘው ግን ከ20ዎቹ የሊጉ ክለቦች 2/3ኛ የሚሆኑት ማለትም 14 ክለቦች ኘሮፖዛሉን ደግፈው ድምፅ ከሰጡ ነው።

ዘአትሌቲክ ከየክለቦቹ አካባቢ ባገኘው መረጃ መሰረት የወልቭስ ጥያቄ ተቀባይነት የሚያገኝ አይመስልም፤ ምክንያቱም አብዛኞቹ የሊጉ ክለቦች ቫር ከሚወገድ ይልቅ ቴክኖሎጂው ተሻሽሎ ተግባር ላይ ቢውል ይመርጣሉ።

የኘሪምየር ሊጉ የዳኞች ቦርድ ሊቀ-መንበር ሀዋርድ ዌብ እንደገለፁት ከቀጣዩ የውድድር ዘመን ጀምሮ በስታድየም የቫር ውሳኔዎችን በይፋ ለህዝብ አብራርቶ የማሳወቅ አሰራር ለመጀመር ሁኔታዎችን በማጤን ላይ ይገኛሉ።

ወልቭስ ኘሮፖዛሉን ሲያስገባ ምንም እንኳን የቫርን ወደሊጉ መምጣት በአዎንታዊ መልኩ የተቀበልነው ቢሆንም በርካታ ያልተፈለጉ ነገሮችን ማስከተሉ በእግር ኳሶ እና በደጋፊዎች መሀል ያለውን ግንኙነት እያሻከረው ይገኛል፤ ይሄ ደግሞ የሊጉን ብራንድ ሊያወርደው ይችላል በሚል ሀሳብ ነበር።

ቫር ከ2019 እ.ኤ.አ ጀምሮ በሊጉ እየተተገበረ ሲገኝ ለተቀላጠፈ የዳኝነት አሰራርም ሆነ ሉውዝግብ በር መክፈቱ የማይካድ ሀቅ ነው።

በመጪውም የውድድር ዘመን ትግበራ ላይ መዋሉ የሚቀጥል ይሆናል።
ዘ አትሌቲክ

ግንቦት 28,2016 አ.ም

SKY ስፖርት ET™

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu