Nav And Top Bar

" ለሪኮርዶች ቅድሚያ አልሰጥም"

ሜሲ ከኢኤስፒኤን ጋር ካደረገው ኢንተርቪው የተወሰደ:

" ህይወቴን ሙሉ የሰራሁትን ከእግር ኳስ ተጫዋችነት ራሴን ለማግለል ዝግጁ አደለሁም፤ መጫወትን እወዳለሁ፤ የእለትእለት ልምምዶችን፣ ጨዋታዎችን እወዳቸዋለሁ። ሁሌም ቢሆን ይሄ ጊዜ እንደሚያበቃ ሳስብ መጠነኛ ፍራቻ ይሰማኛል። ያ ጊዜ ደግሞ እየቀረበ እንደሆነ አውቃለሁ። አሁን ጥሩ ጊዜ እያሳለፍኩ ነው፤ ኳስ ሳቆም የምናፍቃቸውን ጥቃቅን ነገሮችን ሁሉ ሳይቀር እየተደሰትኩባቸው ነው።

" ኢንተር ማያሚ የመጨረሻ እግር ኳስ ክለቤ ነው።"

" የኔ ምርጡ ጎል? ሪያል ማድሪድ ላይ በ2011 ያስቆጠርኩት እና እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነው አለም ዋንጫ ላይ ያስቆጠርኩት ጎል ነው።"

" ማግኘት ምፈልገው ግለሰብ? ማይክል ጆርዳንን አግኝቼው ከሱ ጋር ፎቶ ብነሳ ደስ ይለኛል።"

" አንቶኔላን( ባለቤቱ) ለመግለፅ ቃላቶች ያጥሩኛል። እሷ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነች።"

" ዲቡ ማርቲኔዝ የአለማችን ምርጡ በረኛ ነው።"

" የአለም ሻምፒዮን መሆን ከባድ ነው፤ እናም ሁሉም ሰው ይህንን ዋንጫ አያገኝም፤ ዋንጫው በትክክለኛው ሰአት ነው የመጣው።"

" እኔ ለሪኮርዶች ቅድሚያ አልሰጥም። 6 የአለም ዋንጫ ላይ ተካፈልኩ ለማለት ብቻ አልጫወትም።"

" በእግር ኳስ ሁሉንም ነገር አሳክቼያለሁ።"

" በባርሴሎና ሳለሁ በጋርድዮላ፣ በኤነሪኬ እና በቫልቬርዴ ስር በምሰልጠንበት ጊዜ ደስተኛ ነበርኩ።"

" በፓሪስ ሳለን ቤት ውስጥ ልጆቼ ኳስ ሲጫወቱ የበሩን መጥሪያ ደውለው ኳስ መምታት እንድናቆም ያደርጉን ነበር። ወቅቱ ከባድ ወቅት ነበር።"

" ሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ? ዶርትመንድን ነበር ስደግፍ የነበረው፤ ግልፅ ነው እንደባርሴሎና ደጋፊነቴ ባርሴሎና ፍፃሜ ላይ ከሌለ ተቃራኒውን እደግፋለው፤ የማድሪድ ደጋፊዎችም የሚያደርጉት ነው። ከልጅነቴ ጀምሮ የባርሳ ደጋፊ ነበርኩ፤ ባርሳን እወዳለሁ። በድጋሚ ለሻምፒዮንስ ሊግ መፋለም እንደምንጀምር ተስፋ አደርጋለሁ፤ ዋንጫውን ካሸንፍን ቆይተናል።"

" የአለም ዋንጫን ለሁለተኛ ጊዜ ደርሼ ባጣው እጅግ በጣም ልቤ ይሰበር ነበር፤ ስለ2014ቱ ፍፃሜ በጣም አስብ ነበር። በተከታታይ ይሄኛውን ባጣ ደግም እጅግ ከባድ ይሆናል።"

" የአለም ዋንጫ ፍፃሜ የመጨረሻው ፊሽካ ሲነፋ አላለቀስኩም፤ ነገር ግን ሁሉ ነገር ሲረጋጋ የደስታ እምባ አንብቼያለሁ።"

" ቡድኔን መርዳት እስከቻልኩ ድረስ እና በብቃት መጫወት እስከቻልኩ ድረስ ብሄራዊ ቡድኑን አግዛለሁ። የቡድኑ አካል ሆኜ መቀጠልን እፈልጋለሁ።"

በስተመጨረሻም ሊዮነል ሜሲ የ2026ቱን የአለም ዋንጫ ታሳቢ በማድረግ የጡንቻ ቴራፒዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ይሄን ቃለምልልስ ያደረገለት ኢኤስፒኤን ገልጿል።

ሰኔ 6, 2016 አ.ም

SKY ስፖርት ET™

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu