Nav And Top Bar

ጫማዬን ላውልቅ ወይ ብዬ ጠየኩ

ከ14 ተኛ አመት የልደት በአሌ በፊት ድንቅ ' ሰርኘራይዝ' አጋጠመኝ። አባቴ በሪያል ማድሪድ ካለ ከሆነ ሰው ስልክ ተደውሎለት በውድድር ዘመኑ ረፍት ወቅት ስፔን ሄጄ ልምምድ እንድሰራ መጋበዜ ተነገረው። በጣም ያስገርማል፤ ምክንያቱም ሰውዬው ያለው " ዚዳን ልጅህን ማየት ይፈልጋል" ነው። በዛን ጊዜ ዚዙ የክለቡ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ነበር። ግልፅ ነው ይሄን ስሰማ በደስታ ፈነጠዝኩ፤ ለመሄድ ጓጓሁ።

ነገር ግን ቀላል አልነበረም ምክንያቱም ስካውቶች የኔን ጨዋታ ለመከታተል በፈረንሳይ ባለሁበት አካዳሚ ይመጡ ነበር፤ ሚዲያዎችም የተወሰነ ትኩረታቸውን ለኔ መስጠት ጀምረዋል። 13 አመትህ ሆኖ ደግሞ ያንን እንዴት በአግባቡ መቆጣጠር እንዳለብህ አታውቅም። በጣም ብዙ ጫና ነበር፤ ቤተሰቤም እኔን ከዛ ጫና ለመጠበቅ የተቻለውን አድርጓል።

በዚያን ሳምንት የ14 አመት ልደቴ የሚከበርበት ወቅት የነበረ ሲሆን ያላወኩት ነገር ቢኖር ለካ ቤተሰቦቼ እኔ ወደ ማድሪድ እንድሄድ ከክለቡ ጋር በመሆን ሁሉን ነገር እየጨራረሱ ነው።

አመናችሁም አላመናችሁም ማድሪድ እንደምንሄድ ለማንም አልተናገረንም። ለቅርብ ጓደኞቼ እንኳን አልነገርኳቸውም፤ ምክንያቱም ነገሮች እንደታቀዱት ካልሄዱ ተመልሼ መጥቼ በኔ ስኬት ያገኙትን ደስታ መልሼ ልነጥቅባቸው አልፈለኩም።

ከኤርፖርት ወተን ልምምድ ሜዳ የደረስንበትን አጋጣሚ አልረሳውም። ዚዳን መኪናውን ይዞ በመኪና ማቆሚያ ስፍራ አገኘን፤ በእርግጥም የምታምር መኪና ነበር የያዘው፤ ሰላም ካልነው በኋላ የመኪናው ጋቢና እየጠቆመ እንድገባ ጠየቀኝ፤ እኔም በወቅቱ " ጫማዬን ማውለቅ ይኖርብኝ ይሆን?" ስል ጠየኩት፤ ለምን ይሄን እንዳልኩ አላውቅም ግን በእርግጥም አዎ የዚዙ መኪና ነው( ሳቅ)

ዚዳን እየቀለድኩ ነበር የመሰለው " አረ አይደረግም፤ ና ግባ" አለ እየሳቀ፤ በመኪና ውስጥ ከገባሁ በኋላ ወደልምምድ ማእከሉ ሜዳ እየነዳ ወሰደኝ፤ እኔ በዛ ወቅት አስብ የነበረው " ኦ! የዚዙ መኪና ውስጥ ነኝ" የሚለውን ነው። አስቡት እኔ ከቦንዲ( በፈረንሳይ የምትገኝ አነስተኛ ስፍራ) የወጣሁ ልጅ ነኝ፤ ይሄ እውነት ሊሆን አይችልም፤ አውሮኘላን ውስጥ ተኝቼ እያለምኩ ይሆናል አልኩ ለራሴ።

አንዳንዴ የሆኑ ነገሮችን መኖር ስትጀምሩ የህልም ያህል ይሰማችኋል።

" ለታዳጊ ኪሊያኖች የተፃፈ ደብዳቤ"- ኪሊያን ምባፔ

ከላይ የምትመለከቱትን የምባፔን እና የሮናልዶን ምስል ያነሳው በወቅቱ የክለቡ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር የነበረው ዚነዲን ያዚድ ዚዳን እንደሆነ በቅርቡ የወጣው የተጫዋቹ ' Comic book ' ላይ ይፋ ሆኗል።

ይሀው ዛሬ ምባፔ በይፋ የክለቡ ተጫዋች ሆኗል።

ግንቦት 26, 2016 አ.ም

SKY ስፖርት ET™

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu