Nav And Top Bar

"ትንሽዬዋ 40 ሚሊ ግራም መድሀኒት የህይወቴን እጣ ፈንታ ስትወስን"

ብዙዎች ስለተፈጠረው ነገር የሚያውቁ ይመስላቸዋል፤ ሚያውቁኝም ይመስላቸዋል፤ የጋዜጦችን የፊት ገፅ አይተዋል።

" አንድሬ ኦናና? ኦ! አበረታች ንጥረ ነገር በመውሰዱ ታገደ አደል?፤ እሱ ቀጣፊ ነው፤ እሱ ሱሰኛ ነው" ይላሉ፤ ሁሉም ነገር በይፋ በአለም አቀፉ ስፖርት ገልግል ፍርድ ቤት ከወጣ በኋላ ራሱ እንደዛ ሚሉ አሉ፤ በስሜ ላይ ጥላሸት የቀባ አጋጣሚ...

አንድሬ ኦናና አበረታች ንጥረነገር በመጠቀሙ ታግዷል፤ ይሄን እንዴት ለቤተሰባችሁ ወይም ለልጆቻችሁ ታስረዳላችሁ?

አዎ በእርግጥም ከባድ ነበር፤ ግን ስሙ ማብራሪያ አለኝ። መስማት ከፈለጋችሁ አብራችሁኝ ቆዩ።

" ትንሽዬዋ 40 ሚሊግራም የህይወቴን እጣ ፈንታ ስትወስን" -ኦናና ይናገራል

መስማት ለምትፈልጉ በሙሉ እውነታው ይሄ ነው


በየካቲት 2021 በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁሉን ነገር አጣሁ። በካሜሩን ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር ሳለሁ ከአያክስ ዶክተር ተደወለልኝ። ዶክተሩ ፍሩሴማይድ የተሰኘ መድሀኒት በደሜ ውስጥ መገኘቱን ነገረኝ፤ እኔም " እንዴት? ቀልድ ነው ወይ?" ነበር መልሴ፤ " ዶክ በእርግጠኝነት ሰህተት ሰርተሀል፤ እነዚህ ምርመራዎች እንዴት እንደሚካሄዱ አውቃለሁ። ብዙዎቹን ምርመራዎች አድርጌ ምንም አይነት ችግር አልነበረብኝም።

ፍሩሴማይድ ስለተባለው መድሀኒትም ሰምቼ አላውቅም።

ወደሰውነቴ የሚገቡት መድሀኒቶች ሁሉ ከክለብ ዶክተሮቼ የሚታዘዙ ናቸው። ታዲያ ይሄ ምንድነው? ከአያክስ ጋር ካወራሁ በኋላ ለእጮኛዬ ሜላኒ ደወልኩላት፤ ስለጉዳዩ እየነገርኳት እየሳኩኝ ነበር። ስህተት እንደሆነ እርግጠኛ ነበርኩ። በድንገት " አንድሬ ፍሩሴማይድ ፤ ዶክተሮች ለእርግዝናዬ የሰጡኝ መድሀኒት ነው" አለችኝ።

ያኔ ደነገጥኩ። ያኔ ስህተት እንዳልሆነ አወቅኩ።

ከካሜሩን ስመለስ የክለቡ ዶክተር እና እኔ ወደቤት አመራን። በስተመጨረሻም ራሴን ሲያመኝ እወስደው የነበረውን መድሀኒት ልወስድ ብዬ ፍሩሴማይዱን መውሰዴ ገባኝ፤ ማስቀመጫ እቃዎቹ ተመሳሳይ ናቸው።

ይሄ ትንሽዬ የ40 ሚሊ ግራም መድሀኒት...

በጣም ደንግጬ ነበር፤ አሁንም ቢሆን ግን የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር የሰው ስህተት በሚለው ስር ሊያየው ይችላል፤ ማጣራትም ጀመሩ፤ እኔም ታሪኩን ሙሉ ነገርኳቸው። ብዙ ጊዜ ደጋግመው የጠየቁኝ " እንዴት ይሄ መድሀኒት ቤትህ ሊገኝ ቻለ የሚለውን ነው" ለኔ ለመመመለስ ቀላል የሆነ ጥያቄ ነው። " የእርጉዟ ባለቤቴ መድሀኒት ነው" ቀላል መልስ።

ምንም የፈጠርኩት የፈጠራ ወሬ የለም፤ አልዋሸሁም፤ ሁሉም ማስረጃዎች አሉ። ከምርመራው በኋላ " እሺ እንዲህ አይነት ነገሮች ያጋጥማሉ ፤ በስህተት ነው የወሰድከው፤ ለቀጣዩ ተጠንቀቅ" ይላሉ ብዬ ጠበኩ፤ በእግር ኳሳዊ ቋንቋ ስናስቀምጠው " በቢጫ ያልፉኛል" ብዬ አሰብኩ፤ ሆኖሞ አላለፉኝም በቀጥታ ቀይ ካርዱን መዘዙ። ከየትኛውም እግር ኳስ የ12 ወራት እገዳ።

ኤሬዲቪዜ? ኬኤንቪቢ ዋንጫ? ኢሮፓ ሊግ? ሻምፒዮንስ ሊግ? አፍሪካ ዋንጫ?

ሁሉም ነገር የለም፤ ለእግር ኳስ ተጫዋች አንድ አመት ያለጨዋታ ማለት 10 አመታት እንደማለት ነው፤ ዘላለማዊ ይመስላል።

በእግር ኳስ የምትፈልገውን ነገር ለማሳካት የተገደበ ጊዜ ነው ያለህ፤ ያን ለማሳካት ጠንክረህ መስራት አለብህ፤ እመኑኝ፤ ህልሜን ለመከተል እጅጉን ለፍቻለሁ።
መስዋእትነት ከፍያለሁ።

10 አመቴ ሳለ በሳሙኤል ኢቶ አካዳሚ ለመጫወት ስል ለ4 ሰአታት ከቤቴ ርቄ ተጓዝኩ። ከአንድ ዲያሎ ከተባለ የአካዳሚው አሰልጣኝ ጋር ኑሮን በዛው መጀመሬ ግድ ሆነ።

እስከዛሬው ቀን ድረስ ትንግርት የሚሆንብኝ አካዳሚው እና ዲያሎ አባቴን ከቤት ርቄ እንድሄድ እንዴት እንዳግባቡት ነው። ምንም እንኳን አባቴም የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋች ቢሆንም፤ ሁሌ በትምህርቴ ላይ ትኩረት እንዳደርግ ነው ሚፈልገው፤ ትምህርት ቤት፤ ትምህርት ቤት፤ ትምህርት ቤት፤ ለሱ እግር ኳስ አስተማማኝ የህይወት መንገድ አደለም።

" ብትጎዳስ? ባይሳካልህስ? አይሆንም፤ አይሆንም" ይለኛል።

አንዳንዴ እንደውም ሳሙኤል ኢቶ ራሱ ደውሎ ነው እንዴ ያግባባው እላለሁ( ሳቅ)

በአፍሪካ የነገሮች አሰራር ከአውሮፓ ይለያል፤ ልጅህ ኳስ እንዲጫወት በርቀት ወዳለ ስፍራ መላክ ለአውሮፓውያን እንግዳ ነገር ሊሆን ይችላል፤ እኛ ቤት ገና ከበፊቱ ወንድሜ ኳስ ለመጫወት ወደጃካርታ አቅንቷል። ከድሀ ቤተሰቦች ነው የተገኘነው፤ ስለዚህም አሰራሩን እናውቀዋለን፤ ቤተሰባችሁን ሊረዳ የሚችለውን ህልማችሁን በዚህ መልኩ ነው የምትከተሉት።

አንድሬ ኦናና- " የኦናና እውነታ"

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu