Nav And Top Bar

ምባፔ ማስኩን በጨዋታዎች ላይ መጠቀም አይችልም!

ኪሊያን ምባፔ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ቀለማትን የያዘውን ማስክ አድርጎ ወደሜዳ መግባት እንደማይችል ታውቋል። ቀይ፣ ነጭ እና ሰማያዊ ቀለማትን ያዋሀደው ማስክ የፈረንሳይ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ሎጎም በላዩ ላይ አካቷል።

የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ከህክምና ጋር የተያያየዘ አገልግሎት ከሚሰጡ ማስኮች ቀለም ጋር በተያያዘ ያወጣው ህግ እንደሚያሳየው ከሆነ ማስኩ አንድ ወጥ ቀለም ሊሆን ግድ ይላል። እንደዚህ አይነት ማስኮችን አድርገው ለመግባት ተጫዋቾች ሲዘጋጁም ማህበሩ ማፅደቅ ይኖርበታል።

ዛሬ የታየው የምባፔ ማስክ አንድ ወጥ ቀለም አለመሆኑን ተከትሎም የማህበሩን ፈቃድ ስለማያገኝ ተጫዋቹ በቀጣይ ጨዋታዎች ላይ አንድ ወጥ ቀለም ያለው ማስክ አድርጎ የመግባቶ ግዴታ ውስጥ ይገባል። የፈረንሳይ እግር ኳስ ማህበርም ይሄን ስለተረዳ አንድ ወጥ ቀለም ያለው ማስክ አዘጋጅቶለታል።

ተጫዋቹ በቀጣዩ ጨዋታ ላይ ይሰለፋል አይሰለፍም የሚለው ላይ እስካሁን በግልፅ የታወቀ ጉዳይ የለም።

ዘ አትሌቲክ እንደዘገበው

ሰኔ 13,2016 አ.ም

SKY ስፖርት ET™

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu