Nav And Top Bar

የአውሮፓ የክለቦች ደረጃ እንዴት ይሰላል?

በዛሬው እለት አዲሱ የአውሮፓ ክለቦች ደረጃ ይፋ ሆኗል፤ ታዲያ ይህ ደረጃ እንዴት ይሰላል የሚለውን እናስቃኛችሁ።

የአውሮፓ የክለቦች ደረጃ ሁሌ በየውድድር ዘመኑ መጨረሻ ክረምት ላይ " Update" የሚደረግ ሲሆን ባለፉት አምስት የውድድር ዘመናት ክለቦች ያሳዩት በሀገር ውስጥ እና በኢንተርናሽናል ውድድሮች ያሳዩት ብቃት ከግምት ውስጥ ይገባል። ደረጃው ሲሰላም ክለቦቹ በቅርብ የውድድር ዘመናት ለሰበሰቡት ነጥቦች በስሌቱ ላይ ከፍተኛ መጠን እንዲይዝ ሲደረግ አመቱ አንድ ወደኋላ በቀነሰ ቁጥር የሚሰጠው መጠን( Value) እየቀነሰ ይሄዳል።

የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ( UEFA) የክለቦች ደረጃ ለማስላት ውስብስብ የሆነ ቀመርን የሚጠቀም ሲሆን የተለያዩ ነገሮችን ከግምት ውስጥ ያስገባል፤ ይህም ክለቦቹ በአውሮፓ ውድድሮች( ሀገር ውስጥም/ ኢንተርናሽናልም) ላይ ያሳዩት ብቃት፣ በየትኛው ደረጃ ላይ ከውድድሩ ተሰናብቱ እና ምን ያህል ጨዋታዎች ተጫወቱ ሚለውን ያካትታል። በአውሮፓ ውድድሮች ላይ የተወሰኑ ለውጦች ካሉ ቀመሩ እንደየአስፈላጊነቱ ሊለዋወጥ ይችላል።

ስለስሌቱ የተወሰነ ነገር ለማለት ያህል በአውሮፓ ውድድሮች ላይ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ለክለቡ 2 ነጥብ የሚያስገኘው ሲሆን፤ አቻ መውጣት 1 ነጥብ፤ መሸነፍ ደግሞ 0 ነጥብ ያሰጠዋል፤ በሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ውድድሮች ላይ የሆነ ደረጃ መድረስም ሌላ ነጥብ ያሰጣቸዋል፤ ለምሳሴ ለሻምፒዮንስ ሊግ ማለፍ 4 ነጥብ ሲያስገኝ፤ ጥሎ ማለው መግባት 5 ነጥብ፤ ሩብ ፍፃሜ፣ ግማሽ ፍፃሜ እና ፍፃሜ መድረስም የራሱ የሆነ ነጥብ ያሰጣል፤ ከዚህም በተጨማሪ ወደነዚህ ከፍ ወዳሉ ደረጃዎች መድረስ የራሱ የሆነ የሚያሰጠው የጉርሻ( Bonus) ነጥብ አለ።

በዚህ መልኩ በየውድድር ዘመኑ የተሰበሰቡ ነጥቦች ተደምረውም ከተከታታይ አምስት አመታት ጋር አንድ ላይ ይደመሩና ደረጃው ይሰራል።

ይህ የክለቦች ደረጃ ለምን ይጠቅማል ካላችሁ:

1/ በምድቦች ላይ ጠንካራ ተጋጣሚን ለማስወገድ

አንድ ቡድን ከፍ ያለ የአውሮፓ የክለቦች ደረጃ የሚኖረው ከሆነ የሚመደብበት ቋት ከፍ ያሉት ጋር ስለሚሆን የአውሮፓ ውድድሮች የምድብ ድልድል በሚወጣ ጊዜ ከነዚህ ከባድ ቡድኖች ጋር የመገናኘት እድል አይኖረውም።

2/ ከፍ ያለ የማለፍ እድል

አንድ ቡድን ከፍ ያለ ደረጃ የሚኖረው ከሆነ ተጨማሪ ማጣሪያዎችን ሳያደርግ ወደ አውሮፓ ውድድሮች እንዲያልፍ እድሉ ይኖረዋል።

3/ የፋይንስ ጥቅሞች

አንድ ቡድን ደረጃውን አሻሽሎ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ተገኘ ማለት በአውሮፓ እግር ኳስ ያለውን ወቅታዊ አቋም/ ብቃት የሚያንፀባርቅ ስለሆነ የእይታ አድማሱም በዛው ልክ ይጨምራል። ይህ ደግሞ ከፍ ባለ ዋጋ የአጋርነት ስምምነቶችን እንዲፈፅም፣ የትኬት ዋጋዎች በደንብ እንዲሸጡ እና የተሻለ የንግድ እድሎችን እንዲያገን በር ይከፍትለታል።

ስለአውሮፓ የክለቦች ደረጃ አሰራር በመጠኑም ቢሆን መረጃ እንዳገኛችሁ እናምናለን።

ዛሬ በወጣው የክለቦች ደረጃ መሰረት ማንቺስተር ሲቲ በአንደኝነት ሲቀመጥ፤ ሪያል ማድሪድ በሁለተኝነት፤ ባየርሙኒክ ደግሞ በሶስተኝነት ይከተላል።

SKY ስፖርት ET™

ሐምሌ 5,2016 አ.ም

Yonatan Ayele
Footer
Get In Touch

Yonatan Ayele

yonatan@eskaysportet.com

Follow Us

© SKY ስፖርት ET™. All Rights Reserved.
Developed by Gashu